(ጥቅምት 24/2016 ዓ.ም፤ አርባምንጭ)
ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በብዙ መቶ ሺህዎች ገንዘብ ወጪ በማድረግ በተለያዩ ጊዜያት በአርባምንጭ ማዕከሉ ድሆችን የመመገብ መርሐግብር ሲያከናውን ቆይቷል። ድርጅቱ ይህንን ሰብአዊ ፕሮግራም በማጠናከር በአርባምንጭ ከተማ አቅም ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሐግብር አከናውኗል።
ድርጅታችን በራሱ ሙሉ ወጪ 30 የድሃ ድሃ ቤተሰብ ልጆች ምገባና የመዋዕለ ሕጻናት ትምህርት በመስጠት የነገ ሀገር ተረካቢዎችን የማብቃት ሥራዎች ጭምር እያከናወነ ይገኛል። ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት የድሆች ማዕድ ማጋራት፣ የአልባሳት ድጋፍ፣ ትምህርት እና ለአካል ጉዳተኞች አጋዥ ዊልቼር ድጋፍ በሚሊዮኖች የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ የአርባምንጭ ከተማ መንግስትና ሕዝብን እያገዘ ይገኛል።

