(ሚያዝያ 25/2016 ዓ.ም)
ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት በአርባምንጭ ከተማ ለሚገኙ ሰባ (70) አቅመ ደካሞች ለእያንዳንዳቸው 1 ዶሮ፣ 10 ኪሎ የስንዴ ዱቄት፣ ዘይት እና 10 እንቁላል ድጋፍ አደረገ። የተደረገላቸውን ድጋፍ በአካል ቀርበው የተቀበሉ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ አባላት ከመንግስትና ከድሃው ጎን በመሆን ድርጅቱ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት በአርባምንጭ ከተማና አካባቢው በመንግስት አቅም የማይሸፈኑ የልማት ተግባራት ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር እያከናወነ ይገኛል። ድርጅታችን በአርባምንጭ ከተማ ለሚገኙ ለ100 ቤተሰቦች የ2016 ሙሉ የጤና መድህን ወጪ የሸፈነላቸው ሲሆን በየበዓላቱ ለድሆች በዓይነት ድጋፍ እና በጋሞ ዞን ጤና ልማት የበኩሉን ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል።

