አርባምንጭ፡ ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም (አርባምንጭ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን)
ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት በአርባምንጭ ማዕከሉ ድሆችን የመመገብ መርሐግብር ሲያከናውን ቆይቷል። ድርጅቱ ይህንን ሰብአዊ ፕሮግራም በማጠናከር በአርባምንጭ ከተማ አቅም ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሐግብር አከናውኗል።
ድርጅቱም በራሱ ሙሉ ወጪ 405 የድሃ ድሃ ቤተሰብ ለእያንዳንዳቸው አዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ ለአቅመ ደካሞች ዶሮ፣ እንቁላልና ዱቄት ድጋፍ አድርጓል።

