ጨንቻ ቀን 23/04/2018 ዓ/ም የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት።
በክርስትና እምነት ተከታዮች የሚከበረውን መጭውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ፀሐይ ጎልጎታ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ለ583 በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በመታረም ላይ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ማዕድ ማጋራታቸውን የድርጅቱ መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀሐይ አካሉ ገልፀዋል።
ወ/ሮ ፀሐይ አካሉ በተጨማሪ ማዕዱን ከማጋራት ጎን ለጎን ተቋሙን የጎበኙ ሲሆን በማረም ማነፅ በህግ ታራሚዎች አያያዝና መሰረታዊ ፍላጎታቸው ተሟልቶ አምራች ዜጋ ሆኖ እንዲፈቱ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አድንቀዋል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በአርባምንጭ ከተማ በእርጅናና በጤና እክል ምክንያት ጧሪ ላጡ ተንከባካቢ ለሌላቸው በተለያዩ ማህበራዊ መሰረት ውስጥ ላሉ ሴቶችና ህፃናት እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።
የተቋሙ አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ በበኩላቸው ድርጅቱ ይህንን መልካም አላማ ይዞ በተቋማችን በመገኘት ለታራሚዎቻችን ማዕድ በማጋራቱ በተቋሙና በህግ ታራሚዎች ስም ምስጋና አቅርበው የታሰረውን ጠይቁ የሚለውን የእግዚአብሔርን ቃል በተግባር በመፈፀማችሁ እግዚአብሔር ይስጥልን ብለዋል።

